10 COMMENTS

 1. በለው !ሀቅ እደዚህ ያንቃል ፣ የወያኔ ካድሬዎችና ጋአዜጠኞች ሌላው ሠው እነሱ እንደሚያስቡት እዱያስብ ማሰባቸው በጣም ይገርማል ያሳዝናል ፣ ምንድን ነው ከልባቸው ነው ወይስ ፍርሀታቸው ወይስ የእውቀት ማነስ ነው ? ምን አለ ንግግሩን እስኪጨርስ ቢጠብቀው ፣ ምን አለ ሀሳቡን ሳይቆራረጥ እንዲናገር ቢያደርገው ፣ ወያኔዎች እደዚ አይነት አስተያየቶችን ቢሰሙ ከእውቀት ማነስ የሚሰሩትን ስህተት ሊቀንሱ ይችሉ ነበር ፣ ሁሌም እንደ ገደል ማሚቱ የራሳቸውን ንግግር ብቻ መስማት የሚግጎዳው እራሳቸው ወያኔዎቹን እንደሆነ ማን ይንገራቸው ፣ በተለይ የወያኔ ጋዜጠኞች አእምሮአችሁን ከህሊና እስር በደፍረት አላቁት ፣ የወያኔ ጋዜጠኞች ህሊናችሁን ከፈታቹ የካድሬውም ህሊና ይፈታል ፣ የወያኔ ባለሥልጣኖች ህሊናቸውን እራሳቸው ያሰሩ በመሆኑ እናንተን እግዜር ይፍታቹ ፣ የሞተን ነብስ ይማር ማለት ለናንተ ነው

 2. በጣም አደንቀዋለሁ ጀግና ነው ወተት ነጭ ነው የማለት ያክል እውነቱን ፍንትው አርጎ ነገራቸው ህሊና ላለው ሰው ይህን እውነት መሸሽ አይቻልም

 3. መንግስት የሚቃወሙትን በገፍ እየሰበሰበ ቢያስርም እና ቢገድልም እውነትን ማፈን እንደማይችል እንደ አቶ አናኒያ ሶሪ ያሉ አንበሶች ማረጋገጫ ናቸው።

 4. ይህ ሰው ለሚማገረው ነገር ብሩክ ከበደ እና ሚልዮን ረታ የቃንቃና የ ህግ ተማሬዎ መልስ ልትሰጡ አትችሉም ነገር ግን ጤ ና ይስጥልኝ ሁለታችሁም ወደ ስድስት ኪሎ ስትመጡ ክመምህርነት ነው ችግር የለም ዛሬ እናንተ የዎያኔ ባንዳ ተላላኪ በመሆባቹህ በታም አፍራለው በተለይ ቴዲ አፍሮን አሳልፈህ የሸጥከው ሚሊዎን እና በሩክ ሁለታቹህም የሞጆ ልጆች ዎይስ ባንዳዎች ተላላኪዎች የት እንደምትደርሱ እናያለን ለነገሩ ሚልዮን እንደ ዎያኔ በቁምህ አልቀሃል

 5. እውነት ሲነገርም.እውነት ነው.የወያኔዎቹ.ሲናገሩ.እራሱ.ይርበደበዳሉ.የወያኔ አገዛዝ.ሸቷል.ከርፍቶናል.በቃን ይልቀቅልን..ዘረኝነት አንገፍግፎናል.አማራው ከጉራ.ፈረዳ.ከጅጅጋ.ንብረታቸውን እንኩዋን.መሸጫ.ጋዜ.ሳያገኙ.ውጡ ተብለው.ሲለቁ.12ሺ.ህዝብ.ሜዳላይ ሲወድቅ.ከምንም አልቆጠሯቸው.ዛሬ.ከጎንደር.ከባህር ዳር.በአውሮፕላን.አግዞ ሲጨርስ.የየክልሉን.መንግስታት.እያስገደደ.10ብር.አዋጡ.እያለ.ያመቻችላቸዋል.ታዲያ.ይሄነው.እኩልነት.።

 6. “ከፈለክ ‘ብሄር የለኝም፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ’ ማለት ትችላለህ።” – ዛዲግ አብርሃ (የህወሀት ከፍተኛ ካድሬ)
  እነአናኒያ ሶሪ የተሳተፉበት በሬዲዮ ፋና ሞጋች የተባለ ፕሮግራም በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በተደረገ ውይይት ክፍል 2 ላይ ዘግይቶ የገባው ዛዲግ አብርሃ የተባለ ሁሉም ቦታ የማይጠፋ ካድሬ ብዙ የኢህአዲግ ባህሪያት ያልሆኑ “ደጋግ” ነገሮችን አንስቷል።
  እንግዲህ ዛዲግ አብርሃ ከተናገራቸው ውስጥ በተግባር የሌሉትና ከእውነታ የራቁት ነገሮች አንደኛ ኢህአዲግ ህብረተሰቡን የሚያየው በመደብ መነፅር እንጂ በብሄርተኝነት አይደለም፤ ኢህአዲግ ለመደብ ልዕልና እንጂ ለማንም ልዕልና ያልቆመ ድርጅት ነው የሚለው።
  ሁለተኛ ኢህአዲግ ከማንም በፊት አስቀድሞ ለኤርትራ ነፃነት እውቅና የሰጠው ለህዝብ የቆመ ድርጅት በመሆኑ ነው የሚለው።
  ሶስተኛ ከኢህአዲግ በፊት በነበሩት መንግስታት “አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ። አማራ አይደለህም፤ ኦሮሞ አይደለህም፤ ትግሬ አይደለህም” ተብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ብሄረሰቦች ሁሉ ማንነታቸው እውቅና አልነበረውም የሚለው።
  አራተኛ በኢትዮጵያ ውስጥ ኢህአዲግ ላመጣው ዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አለመሳካት ሌሎችም አካላት (ቤተሰብ፥ ማህበረሰብ፥ ትምህርት ቤቶች፥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወዘተ) ተጠያቂ ናቸው የሚለው።
  አምስተኛ በኢህአዲግ ዘመን አንድ ሰው ከፈለገ ‘ብሄር የለኝም፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ’ ማለት ይችላል፤ በግድ ብሄር መምረጥ አለብህ ብሎ ሰው አይገደድም፤ በሰነዶቹና በተግባርም ኢህአዲግ እንደዚያ የሚያደርግ ድርጅት አይደለም የሚለው እና ወዘተ ናቸው።
  ከዛዲግ አብርሃ ንግግሮች በተለይ በአምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠውን ያነበበ “ብሄር የለኝም፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚል ሰው ከዛሬ ጀምሮ ቀበሌ መታወቂያው ላይ “ኢትዮጵያዊ” የሚል ማፃፍ ይችላል። እውነት እንደዚያ ማድረግ ከተፈቀደ ያኔ የኢህአዲግ የ”ጥልቅ ተሃድሶ” ውጤት አድርገን እንመዘግበዋለን።
  በነገራችን ላይ አናኒያ ሶሪን በክፍል አንድ 3 ለ 1፥ በክፍል ሁለት 4 ለ 1 በጥርነፋ ገጥመውት ሳይ በየቦታው የህወሃት/ኢህአዲግ ወታደሮች አንድን ሲቪል ከበው በጭካኔ የሚደበድቡት ድርጊት ትውስ አለኝ። ለማንኛውም ሰዎቹ የሚለወጡ ባይሆኑም አናኒያ ግን በትንሹም ቢሆን ልክ ልካቸውን በመናገር ቢያንስ የውስጡን ስሜት አውጥቶ ተናግሮ ወጥቶለታል። ፋኑኤል ክንፉ የተባለው ተወያይም በተቻለው መጠን ሚዛናዊ አስተያየት ለመሰንዘር ሞክሯል።
  ማሳሰቢያ፦ አብዛኛው የዛዲግ አብርሃ ንግግር በእንግሊዘኛ ቃላት “ያሸበረቀ” ስለሆነ ቋንቋውን የምትችሉ እባካችሁ እየተረጎማችሁ ለየቀበሌያችሁ ነዋሪዎች መልዕክቱን አስተላልፉ።

LEAVE A REPLY